Senior Sales Team Lead
Duties/Responsibilities: Provides leadership to the sales team. Motivates and encourages sales team to ensure quotas are met. Reviews and analyzes sales and operational records and reports; uses data to project sales, determine profitability and targets, and identify potential new markets. Identifies and analyzes customer preferences to properly direct sales efforts. Assigns territories and sets quotas […]
ጊዜ ወስደው ስብሰባው ላይ ለተካፈሉ ባለአክሲዮኖቻችን ፣የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደርገላችሁ የመንግስት አካላት እና የዝግጅቱ አካል ለነበሩ የመስሪያ ቤታችን ሰራተኞች በሙሉ በዚህ አጋጣሚ ምስጋናችንን ለመግለጽ እንወዳለን።
በአንድ ዓመት ውስጥ ትርፋማ ከመሆን በተጨማሪ፣ድርጅታችን ትልቅ አቅም ያለው እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል ከነዚሀም መካከልም መዋቅራዊ ዝግጅት፣ የቢሮ ማስፋፋት፣ የመሰረተ ልማት ዝግጅት፣ ስልታዊ አቅጣጫዎች መንደፍ እና የአብሮነት/Engagement Framework/ ዝግጅት ይገኑበታል።
ቀጣዮቹ ዓመታት ድርጅታችን የላቀ ውጤት ለማምጣት የተቀመጠውን ርዕይ እና ተልእኮ መሰረት በማድረግ በቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪው ውስጥ የመሪነት ሚናውን ለመጫወት እና ወደ ገበያው ዘልቆ ለመግባት የሚያስችለውን ስልታዊ እቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
በያዝነው ዓመትም በዓለም አቀፍ ደረጃ በዘርፉ የሚከናወኑ የቴክኖሎጅ ስራዎች ላይ ለመሳተፍ ይረዳን ዘንድ ከሀገር ውጪ በአሜሪካ እና በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ዱባይ ላይ ቢሮዎችን ለመክፈት እየሰራን እንገኛለን።
ለነባር ባለአክሲዮኖቻችን ቀደም ብለው በያዙት አክሲዮን መጠን የመጀመሪያ ክፍያ ቢያንስ 25 በመቶውን በመክፈል እስከ ሰኔ 23 ቀን 2014 ድረስ ኢንቨስትመንታቸውን በእጥፍ እንዲያሳድጉ እድል ተሰጥቷል። እንዲሁም የኢቴክ አክሲዮን ማኀበር አባል ለመሆን ለምትሹ አዳዲስ ባለአክሲዮኖች ወደፊት ለባለአክሲዮኖች የተሰጠውን እድል የማይጠቀሙ ባለአክሲዮኖች ካሉ ለአዲስ ባለአክሲዮኖች የምንሸጥ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን።